አብዘሃኞቻች በዕየለቱ ከምጠቀምባቸዉ የትራንስፖርት አይነቶች የከተማ ታክሲዎች ዋነኛዎቹ ናቸዉ ፡፡ ለዛረዉ የምንታዘብ እነርሱን ቢሆንስ?
እዚህ ጎንደር ከአራዳ ፣ፒያሳ ፣ አዉቶ ፓርኮ ፣ማራኪ …………… አዘዞ ወዘተ መንቀሳቀስ ብትፍልጉ በታክስ መጓዝ ግድ ነዉ ፡፡ በለገራችን ላይ ጎንደር እንደሌሎች ከተሞች ሁሉ የጣሊያን ስሞች ይበዛሉ ለምሳሌ ፒያሳ ፣ ብልኮ ፣አዉቶ ፓረኮ ፣………. እናም ካሉት ታክሲዎች በአንዱ ተሳፍረዉ ሲጓሁ 13 ሰዉ እንዲጭን የተፈቀደለት ታክሲ 18 ሰዉ እና ከዚያ በላይ መጫን የተለመደ ነዉ እናም እርስዎ እንደፈረደብዎ ዎይ 2 ሰዉ ይሸካማሉ ወይ ደግሞ ሰዉ ይሸከመዎታል እንዲህ ሆነዉ እየተጓዙ እንድ ነገርሊታዘቡ ይችላሉ ይሀዉም ከፊት /ጋቢና/ የሚጫን እንድ ሰዉ ብቻ መሆኑን ለምን ብለዉ ከጠየቁ ሾፌሩን ይመቀዋል እና እርስዎ እዛዉ ይቃጠሉ በብሎ ይነገረዎታል ፡፡ ለደንበኛ እርካታ መስራት ይሉታል ይህ ነዉ?